Fana: At a Speed of Life!

አስቶንቪላ አሰልጣኝ ስቴቨን ጄራርድን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ አስቶንቪላ አሰልጣኝ ስቴቨን ጄራርድን ማሰናበቱን አስታወቀ።

ክለቡ ትናንት ምሽት በለንደኑ ክለብ ፉልሃም ጋር ባደረገው ጨዋታ 3 ለ 0 መሸነፉን ተከትሎ ነው አሰልጣኙን ያሰናበተው።

ጄራርድ በፈረንጆቹ 2021 ጥቅምት ወር ወደ ቪላ ፓርክ በመምጣት አስቶንቪላን ማሰልጠን የጀመረ ሲሆን በተጠናቀቀው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር አመት ክለቡ 11ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል፡፡

በዘንድሮው የሊጉ የውድድር አመት ደግሞ ክለቡ በውጤት ቀውስ ላይ  የሚገኝ ሲሆን ከ12 ጨዋታዎች ሁለቱን ብቻ በማሸነፍ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

የቀድሞው የሊቨርፑል ኮከብ በስኮትላንዱ ሬንጄርስ በአሰልጣኝነት ስኬታማ ጊዜን ካሳለፈ በኋላ በእንግሊዙ ክለብ ያሰበውን ማሳካት አልቻለም።

በፕሪሚየር ሊጉ ከእርሱ ቀደም ብሎ ስኮት ፓርከር ከበርንማውዝ፣ ቶማስ ቱሼል ከቼልሲ እንዲሁም ብሩኖ ሌጅ ከወልቨርሃምፕተን ወንደረርስ ከአሰልጣኝነት መሰናበታቸው ይታወሳል።

የቀድሞው የቶተንሃም ሆትስፐርስ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ እና ከቼልሲ የተሰናበቱት ቶማስ ቱሼል ጄራርድን ይተካሉ በሚል ከክለቡ ጋር ስማቸው መያያዙን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.