Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የጋራንባ ተራራ ማህበረሰብ አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የጋራንባ ተራራ ማህበረሰብ አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻን መርቀው ከፍተዋል፡፡

አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚሁ ወቅት ÷በሀገር አቀፍ ደረጃ ለቱሪዝም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው ክልሉ ይህን ተከትሎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የሲዳማ ክልልን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የጋራንባ ተራራ የማህበረሰብ አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻን መርቀን ለቱሪዝም ክፍት አድርገናል ነው ያሉት፡፡

የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጀጎ አገኘሁ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ክልሉ በቱሪዝም ዘርፍ አበረታች ውጤት እያመጣ ነው፡፡

የቱሪዝም ሀብትን ለማልማት በክልሉ ያሉትን የቱሪዝም ሀብቶች በጥናት የመለየት ስራ መሰራቱንም ጠቅሰውዋል፡፡

የጋራንባ ተራራ ላይ የቱሪዝም መዳረሻ ለመስራት ክልሉ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸው÷ስፍራው ሲለማ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል፡፡

ተራራው በክልሉ አርቤጎና ወረዳ የሚገኝ ሲሆን÷ ከባህር ጠለል በላይ 3 ሺህ 382 ከፍታ አለው ነው የተባለው፡፡

በጥላሁን ይልማና ደብሪቱ በዛብህ

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.