የሀገር ውስጥ ዜና

የኳታሩ ስሀይል የብረት ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

By Tibebu Kebede

November 04, 2019

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኳታሩ ስሀይል የብረት ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።

ኳታር የሚገኙት የኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዛሬው እለት የኩባንያውን የብረታ ብረት እና የባትሪ ማምረቻ ፋብሪካዎች መጎብኘታቸውን በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።