Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች በቦነስ አይረስ የአፍሪካ ሀገራት ከንቲባዎች ባደረጉት መድረክ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ ከተማ እየተካሄደ ባለው የሲ40 የአለም ከንቲባዎች ፎረም ጎን ለጎን የአፍሪካ ሀገራት ከንቲባዎች መድረክ ተካሂዷል።

በፎረሙ እየተሳተፉ ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ መድረክ ተሳትፈዋል።

መድረኩ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ላይ በጎ ተፅእኖ የሚያሳድር የአየር ንብረት እንዲኖር በሚያደርጉ መንግስታዊ ተነሳሽነቶችና በጎ ተሞክሮዎች ዙርያ ነው የተካሄደው።

በመድረኩ ከአክራ ፣ ኬፕታውን፣ ዳካር፣ ዳሬሰላም እና ሌሎች ታላላቅ ከአፍሪካ ከተሞች የመጡ ከንቲባዎች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤም ለሀገራቱ ከንቲባዎች የኢትዮጵያን ተሞክሮ ማካፈላቸው ተገልጿል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ የቆሻሻ አወጋገድ እና መልሶ መጠቀም ስርዓት ገንብታ በአለም አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ በመሆኗ በእጅጉ እንዳስደሰታቸው የአፍሪካ ከንቲባዎች በመድረኩ ላይ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ከንቲባዋ በቆይታቸው ከለንደኑ ከንቲባ ሳዲቅ ካሀን እና የC40 የአፍሪካ ዳይሬክተር ከሆኑት ሀስቲንግስ ቺኮኮ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.