Fana: At a Speed of Life!

በ22 ሚሊየን ብር ወጪ የሚተገበር የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ አገልግሎት ማሻሻያ ኘሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22 ሚሊየን ብር ወጪ በ8 ክልሎች የሚተገበር የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ አገልግሎት ማሻሻያ ኘሮጀክት ይፋ ሆኗል፡፡

“አምሪፍ ኼልዝ ኢትዮጵያ እና ጂ ኤስ አይ” በተሰኙ አጋር ድርጅቶች ቅንጅት የሚተገበረው  ፕሮጀክቱ  በአምስት ዓመታት ውስጥ  በ44 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በሀዋሳ ይፋ በተደረገው ፕሮጀክት ላይ የተገኙት የጤና  ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ÷የዚህ ፕሮጀክት ይፋ መሆን ከአመት በፊት ፀድቆ ወደ ስራ የገባውን የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአምሪፍ ኼልዝ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ስንታየሁ ፀጋዬ በበኩላቸው÷ የፕሮጀክቱ ተግባራዊ  መሆን በአገር አቀፍ ደረጃ መንግስት የጤናውን ዘርፍ ለማሻሻል እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት ያግዛል ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚተገበር ከመሆኑም በላይ በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ የሚያተኩርና የጤና ተቋማትንና የህብረተሰቡን መደጋገፍ የሚያጠናክር ነው መባሉን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.