Fana: At a Speed of Life!

የምዕራባውያንን ጣልቃገብነት የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ በድሬዳዋ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬደዋ ነዋሪዎች የምዕራባውያንን ጣልቃገብነት የሚቃወምና መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ  ህዝባዊ ሰልፍ በድሬዳዋ ተካሂዷል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ  ከድር ጁሃር ለሰልፈኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ከውስጥም ከውጭ የተደቀኑብንን  ጦርነትና ጫና በማሸነፍ የጠላቶቻችን ቅስም መስበር ችለናል ብለዋል፡፡

ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና አጥብቀን እንቃወማለን ያሉት ከንቲባው፥ ነዋሪዎቹ በኢትዮጵያ ላይ የሚደርሰውን ጫና በመቃወም መከላከያ ሰራዊቱን እንዲደግፉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በድሬዳዋ ውስጥ የሚገኙ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክክር ቤት ሰብሳሲ አቶ ዬናስ በትሩ በበኩለቸው፥ በአንድ አገር ውስጥ ሁለት ሰራዊት መኖር ሰለማይቻል ህወሃት ትጥቁን በመፍታት ወደ ሠላም መመለስ አለበት ብለዋል፡፡

በተለይ ምዕራባውያን በእርዳታ ስም በሀገራችን ላይ እያደርሱ ያለውን ጫና እንቃወማዋለን ብለዋል፡፡

ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ድምፄን አሰማለሁ በሚል መሪ ቃል ከአስተዳደሩ ገጠርና ከተማ የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች  እና የሲቪክ ማህበራት በሰልፉ ተሳትፈዋል፡፡

በምንያህል መለሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.