Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የአቪዬተርስ አፍሪካ ሽልማት ተሸለሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ አርአያ ለሆኑ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚሰጠውን የአቪዬተርስ አፍሪካ ሽልማት ፕሮግራም በለውጥ ፈጣሪዎች ምድብ ተሸለሙ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተካሄደው 4ኛው የአቪዬተርስ አፍሪካ ሽልማትና እውቅና መድረክ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በሰጡት የላቀ የስራ አመራር በለውጥ ፈጣሪዎች ምድብ ተሸላሚ መሆናቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በአቬዬሽን ኢንዱስትሪው ለአፍሪካ የአቪዬሽን እድገት አስተዋፅኦ ላበረከቱ እና ለውጥ ፈጣሪዎች እውቅና የሚሰጥበት የአፍሪካ ሀገር በቀል ሽልማት የሆነው የአቪዬተርስ አፍሪካ ሽልማት (ታወር ሽልማት) የአፍሪካ አቪዬሽን ዘላቂነት በሚል መሪ ሐሳብ ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የአቬዬሽን ኢንዱስትሪው ደኅንነቱ ተጠብቆ እንዲንቀሳቀስ በሰጡት አመራር እና በዘርፉ ለውጥ እንዲመጣ ለተጫወቱት የላቀ ሚና እውቅና ተበርክቶላቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.