በሐዋሳ የብስክሌተኞችና የእግረኞች ጉዞ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “በትራፊክ አደጋ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ እኔም ድርሻ አለኝ” በሚል መሪ ሐሳብ በሐዋሳ ከተማ ሀገር አቀፍ የብስክሌተኞችና የእግረኞች ጉዞ ተካሂዷል፡፡
በጉዞው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ እና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ጉዞው የተካሄደው በጭስ አልባ ተሽከርካሪዎችና በእግር ጉዞ ነው።
የሞተር አልባ ትራንስፖርት በብስክሌትና በእግር የመጓዝ ባህልን በማዳበር ምቹና ጭስ አልባ ከተማን መፍጠር ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በታሪኩ ለገሰ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!