የሀገር ውስጥ ዜና

በምሥራቅ ሐረርጌ በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

October 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ እንደገለፁት÷ ትናንት ከምሽቱ 4፡45 አካባቢ በግራዋ ወረዳ ቢቢዮ መገንጠያ አካባቢ ከሐረማያ ወረዳ ኢሬሳ ወደ መዪ ወረዳ ሲጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ ተገልብጦ የአራት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ በአደጋው በአንድ ሰው ላይ ከፍተኛ እና በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱንም ነው ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ለፋና ብሮድካስንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡

አሸከርካሪው ለጊዜው ከአካባቢው መሰወሩን እና የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!