ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ ለ3ኛ ጊዜ ቻይናን እንዲመሩ ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ለሦስተኛ ጊዜ ሀገራቸውን እንዲመሩ ተመርጠዋል፡፡
ለሦስተኛ ጊዜ መመረጣቸውን ተከትሎም አዲሱን ካቢኔያቸውን ማዋቀራቸው ተሰምቷል፡፡
ፕሬዚዳንት ሺ÷ ከቀድሞው የቻይና ኮሚኒስት መሪ ማኦ ዜዱንግ በኋላ የሀገሪቱ ኃያል መሪ መሆናቸውን ለሦስተኛ ጊዜ የመሪነት ቦታውን በመቆናጠጥ ማረጋገጣቸውን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
የዜሮ ኮሮና እንቅስቃሴያቸው እና ሌሎችም በየዘርፉ ያስመዘገቧቸው ስኬቶች በሳል መሪነታቸውን የሚገልፁ መሆናቸውንም ዘገባው አመላክቷል፡፡