የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 11 ሰዎች መካከል ሁለቱ ጃፓናውያን ወደ ሃገራቸው ተሸኙ

By Tibebu Kebede

March 23, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 11 ሰዎች መካከል ሁለቱ ጃፓናውያን ወደ ሃገራቸው መሸኘታቸውን አስታወቀ።

ሌሎች በቫይረሱ የተያዙ እና ከሰዎቹ ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉ ሰዎችም ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ነው የተባለው።

ከዚህ ቀደም በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መካከል አራቱ የህመም ስሜት ማሳየት ማቆማቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ መግለጻቸው ይታወሳል።

የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልም ከዛሬ ጀምሮ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ሰዎች በግዮን እና ስካይ ላይት ሆቴሎች ለ14 ቀናት ወደ ለይቶ ማቆያ ማስገባት ግዴታ ተጀምሯል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision