Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ስታስቲክስ ዳይሬክተሮች ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 8ኛው የአፍሪካ ስታስቲክስ ዳይሬክተሮች ጉባዔ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ጉባዔው÷“ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከርና ለመደጋገፍ በአፍሪካ የመረጃ አያያዝን ማዘመን” በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ፔድሮ በጉባዔው ላይ እንደገለጹት ፥ የወሳኝ ኩነት መረጃ የአፍሪካን ዘላቂ እድገትና የአፍሪካ ሕብረትን አጀንዳ 2030 እና 2063 ለማስፈጸም እጅግ አጋዥ ነው።

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት የወሳኝ ኩነት መረጃዎችን ለመያዝ ችግር ማጋጣሙን ጠቁመው÷ ባለፉት አስር ዓመታት በዘርፉ ስኬታማ ሥራ ተሠርቷል ነው ያሉት፡፡

ባለፉት ዓመታት በአፍሪካ ከፍተኛ አመራሮች ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት ማድረግና የዘርፉ ባለሙያዎችን ማብቃት መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በመድረኩ ላ ይ ባደረጉት ንግግር÷ በአፍሪካ ዘላቂ እድገት ለማምጣት የተለያዩ ፖሊሲዎችን ለማውጣትና ውሳኔዎችን ለመወሰን የወሳኝ ኩነት መረጃ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የወሳኝ ኩነት መረጃን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በዘመናዊ መንገድ መያዝ መጀመሩን ጠቅሰው÷ የወሳኝ ኩነት መረጃን ለግብር ዘርፍ ጭምር ማዋል ተችሏል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትም ለብሔራዊ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መዘመን የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ አረጋግጠዋል፡፡

ትኩረቱን በአፍሪካ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ላይ ያደረገው አህጉራዊ ውይይት ለስድስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ ከኮቪድ-19 በኋላ በአካል ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው።

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.