የኦሮሚያ ክልል የ2015 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል የ2015 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ፣ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ፍቃዱ ተሰማን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ በክልሉ የሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች አመራሮች እንዲሁም የቢሮ ሃላፊዎች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡
በመድረኩ በበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ላይ በተስተዋሉ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም ሌሎች ጉዳች ላይ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!