Fana: At a Speed of Life!

ቦሪስ ጆንስን የእንግሊዝ ወግ አጥባቂ ፓርቲን ለመምራት ከሚደረገው ፉክክር ራሳቸውን አገለሉ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንስን ወግ አጥባቂ ፓርቲን በድጋሚ መምራት ከሚያስችላቸውው ፉክክር ራሳቸውን አግልለዋል።

ውሳኔውን ተክትሎ ቦሪስ ጆንስን ሊዝ ትረስን በመተካት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደማይመጡ ተረጋግጧል ነው የተባለው፡፡

የቦሪስ ጆንሰንን ውሳኔ ተከትሎ የቀድሞውን የፋይናንስ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እና የእንግሊዝ ፓርላማ መሪ ፔኒ ሞርዳውንት ለፓርቲው ሊቀ መንበርነት ምርጫ ተፎካካሪዎች ሆነው ቀርበዋል።
አሁን ላይ እየወጡ ባሉ መረጃዎችም ሪሺ ሱናክ ተሰናባቿን ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስን ለመተካት ሰፊ ግምት ማግኘታቸው ተሰምቷል፡፡

ዛሬ ከሰዓት ይጠናቀቃል በተባለው ምርጫ ፔኒ ሞርዳውንት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ምርጫውን ለማሸነፍ ደጋፊዎችን እያሰባበሰቡ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.