Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮምና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ክፍያን በቴሌብር አማካኝነት ለመክፈል የሚስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሰረትም ደምበኞች በቴሌብር አማካኝነት ያለምንም ተጨማሪ ወጪ ክፍያቸውን ባሉበት ቦታ ሆነው መክፈል ያስችላቸዋል ነው የተባለው፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ÷ ስምምነቱ የደንበኞችን ድካም እንደሚቀንስ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው÷ኢትዮ ቴሌኮም ተቋማት በቴክኖሎጅ ተደግፈው ጥሩ የአሰራር ሂደት እንዲኖራቸው እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም ማህበረሰቡ ክፍያውን በቴሌብር አማካኝነት በመክፈል ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ አንዱ ነው ብለዋል።

ከሚኒስቴሩ ጋር በቀጣይም አብረን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት ከ87 በላይ ተቋማት በቴሌብር አማካኝነት የተለያዩ ክፍያዎችን እየፈፀሙ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.