Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በእንጦጦ የስነ ጥበብ ማዕከል የተዘጋጀውን የቨርቹዋል ኤግዚቢሽን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእንጦጦ የስነ ጥበብ ማዕከል የተዘጋጀውን የቨርቹዋል ኤግዚቢሽን ጎበኙ።
 
ኤግዚቢሽኑ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን በቨርቹዋል ያስጎበኛል።
 
ይህ ባለፈው መስከረም ወር ላይ የተከፈተው ኤግዚቢሽን፥ አዲስ አበባ ላይ በመሆን የላሊበላን ውቅር አብያተ ክርስቲያንት በአካል ተገኝቶ የመጎብኘት ያክል ምስል ከሳች በሆነ መንገድ ለመጎብኘት የሚያስችል ነው።
 
የኢትዮጵያ መንግስት ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ ኤግዚቢሽን በዓይነቱም በሀገራችን የመጀመሪያው ስለመሆኑ ተገልጿል።
 
በኤግዚቢሽኑ በዋናነት ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ እንዴት እንደተገነቡ፣ ውስጣዊ እና ውጫዊ ገፅታቸውን በምስል እና በድምፅ ዳብሮ ቀርቦበታል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጉብኝቱ በኋላ እንደተናገሩትም፥ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በዚያ ወቅት ያለውን የማለም አቅም የሚያሳይ ነው።
 
አንድ ሰው ያለመውን ህልም በጋራ ወደመሬት አውርዶ እውን አድርጎ የማሳየት አቅምም እንደዚሁ የሚንፀባረቅበት እንደሆነ ነው ያመለከቱት።
 
አሁን ያለን ኢትየጵያውያንን ከዚህ ተምረን መስራት ይኖርብናል ብለዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ኤግዚቢሽኑን ኢትዮጵያዊያን መጥተው እንዲመለከቱም ነው ጥሪ ያቀረቡት።
 
በአልዓዛር ታደለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.