ሱናክ ቀጣዩ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸውን አረጋገጡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሪሺ ሱናክ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ሱናክ ተሰናባቿን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብሪታንያ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ሊቀ መንበር ሊዝ ትረስን ለመተካት ይሁንታን አግኝተዋል።
የሱናክ ተቀናቃኝ ሆነው የቀረቡት ፔኒ ሞርዳውንትም ራሳቸውን በማግለል ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ወግ አጥባቂ ፓርቲን ለመምራት ብቸኛ እጩ ሆነው መቅረባቸውን ተከትሎ ነው ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸውን ያረጋገጡት።
ሪሺ ሱናክ ከህንዳውያን ቤተሰቦች በሳውዝሃምፕተን ከተማ የተወለዱ ሲሆን የእንግሊዝ ወግ አጥባቂ ፓርቲ አባል በመሆን ከፈረንጆቹ 2019 እስከ 2020 የእንግሊዝ ፋይናንስ አስተዳደር ሃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡
በእንግሊዝ የተስተዋለው የዋጋ ግሽበትን ማስተካከል የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተቀዳሚ ተግባር እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ባለፈው ሳምንት ቦሪስ ጆንሰንን በመተካት ወደ ስልጣን የመጡት ሊዝ ትረስ ከ44 ቀናት የስልጣን ቆይታ በኋላ ስልጣን መልቀቃቸው የሚታወስ ነው፡፡
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለእንግሊዝ ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪነት ከሚደረገው ፉክክር ራሳቸውን ማግለላቸውም ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!