በፕሪሚየር ሊጉ የተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ዛሬ የተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል፡፡
ቀደም ሲል በምሳ ሰዓት ጨዋታቸውን ያደረጉት ሀዋሳ ከተማ እና ድሬዳዋ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል፡፡
የሀዋሳ ከተማን ግቦች ላውረንስ ላርቴ እና አሊ ሱለይማን ሲያሰቆጥሩ÷ ቢኒያም ጌታቸው ደግሞ የድሬዳዋን ሁለቱን ግቦች በስሙ አስቆጥሯል፡፡
10 ሰዓት የተደረገው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ በተመሳሳይ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
ሄኖክ ኤለ እና አብነት ደምሴ የኢትዮ ኤሌክትሪክን ሁለት ግቦች ሲያስቆጥሩ÷ መሱድ መሀመድ እና አብዲሳ ጀማል ደግሞ የአዳማ ከተማን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡