ብሔራዊ ባንክ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ ባንክ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በጸደቀው የባንክ ስራ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እና የዳያስፖራ ረቂቅ አዋጅላይ እየተወያየ ነው።
ውይይቱ ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ነው እየተካሄደ ያለው።
ውይይት የሚደረግባቸው እና የግብአት ሀሳብ የሚቀርብባቸው ሰነዶች በዋናነት በባንክ እና ኢንሹራንስ ዘርፉ ላይ እውቀት፣ ክህሎት እና ቴክኖሎጂዎችን ለማስፋፋት እንደሚያግዙ ታምኖባቸዋል።
ከዚህ ባለፈም ቀልጣፋ እና ተወዳዳሪ ሆኖ ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ዘርፉን ለሀገሪቷ ዕድገት በሚመጥን መልኩ ማሳደግ ያስችላሉም ነው የተባለው።
በአዲሱ ሙሉነህ