የሀገር ውስጥ ዜና

16ኛው የኢትዮ ጅቡቲ የጋራ ሚኒስትሮች ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

By Amele Demsew

October 25, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የኢትዮ ጅቡቲ የጋራ ሚኒስትሮች ስብሰባ በባለሙያዎች ደረጃ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ስብሰባው ከዛሬ ጥቅምት 25 እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2022 ዓ.ም እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ስብሰባው በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የመሰረተ ልማትና የሎጂስቲክስ ትብብር ላይ ያተኩራል ነው የተባለው።