የሀገር ውስጥ ዜና

ባሕርዳር የማዕድን ኢንቨስትመንትና ልማት የንቅናቄ መድረክ እያስተናገደች ነው

By Alemayehu Geremew

October 25, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የማዕድን ኢንቨስትመንትና ልማት ንቅናቄ መድረክ በአማራ ክልል ባሕርዳር እየተካሄደ ነው።

የክልሉን የማዕድን ሐብቶች የተመለከተ ምክክር እየተካሄደ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በውይይት መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ የዘርፉ ባለ ድርሻዎች ተገኝተዋል።

እየተካሄደ በሚገኘው የማዕድን ኢንቨስትመንትና ልማት ንቅናቄ መድረክ ላይ በአማራ ክልል ከ24 በላይ የማዕድን አይነቶች እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

በክልሉ የሚገኙትን ማዕድናት የሚያሳይም አውደ-ርዕይ ተከፍቷል።

በአማራ ክልል ለኮንስትራክሽን ግብዓት ፣ ለኢንዱስትሪ እንዲሁም ለኢነርጂ አገልግሎት የሚውሉ የከበሩ ማዕድናት በስፋት ይገኛሉም ተብሏል።

በዓለምሰገድ አሳዬ