የመከላከያ ሠራዊት ቀን በተለያየ መርሐ ግብር እየተከበረ ነው

By Meseret Awoke

October 25, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሠራዊት ቀን በተለያየ መርሐ ግብር እየተከበረ ነው።

“የእሳት ቀለበት የህግ ማስከበር ዘመቻ ንፍቀ መዋዕል” በሚል ርዕስ የተጻፈ መጽሐፍ ዛሬ እየተመረቀ ነው።

መጽሐፉ በዋና አዘጋጅ፣ በአዘጋጅና በረዳት አዘጋጅነት የተጻፈ 360 ገጽ ያለው ነው።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የቀድሞ የኢፌዴራ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል።

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ ባደረጉት ንግግር÷ ሠራዊቱ እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት በማሰብ ለዚሁ ምስጋና እያቀረብን እና ስለ ጀግንነታቸው እየዘከርን የምናሳልፈው ቀን በሠራዊቱ ስም ተሰይሟል ብለዋል፡፡

በቆንጂት ዘውዴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!