Fana: At a Speed of Life!

እየተመዘገቡ ያሉ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊና ከተማዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ መለሰ ዓለሙ እንደገለጹት ለሁለት ቀናት በሚቆየው መድረክ ላይ÷የደም ዋጋ እየተከፈለበት የዘለቀውን ነፃነታችንን በላባችን ለማስቀጠል በኢኮኖሚ፣ በዲሞክራሲ እና በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችን ለማፅናት በሚያግዙ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡

በሀገር ሉዓላዊነት እና ነጻነት የታየው አንድነት በልማት ሥራዎች ሊደገም እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

አመራሩ ለሕዝቡ ምላሽ ለመስጠት ቃል የገባቸውን አንገብጋቢ ጥያቄዎች ከመፍታት አንፃር ያሉ ስኬቶችና ተግዳሮቶች እንዲሁም መፍትሄዎቻቸው በውይይቱ ይዳሰሳሉ መባሉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.