የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ ለሚኖሩ አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ተከፋፈሉ

By Feven Bishaw

March 23, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከባለሀብቶች፣ ከተለያዩ ተቋማት እና ከበጎ ፈቃደኞች የተሰባሰበው ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ተከፋፈሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን አስቀድሞ ለመከላከል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ ከባለሀብቶች፣ ከተለያዩ ተቋማት እና በጎፈቃደኞች ያሰባሰባቸው ናቸው።

የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ የተደረገላቸው በ116 ወረዳዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ነዋሪዎች ናቸው።

በተጨማሪም ከ24 በላይ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበራት እንዲሁም የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከላት የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ እንደተደረገላቸው ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።