Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ እና አፍጋኒስታን የኮሮና ቫይረስ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ መቀነስ የሚያስችል ድጋፍ ሊያጸድቅ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ40 ሃገራት የኮሮና ቫይረስ የሚያደርሰውን ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ መቀነስና መከላከል የሚያስችል የ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ድጋፉ ኢትዮጵያና አፍጋኒስታንን ጨምሮ በሃገራቱ የኮሮና ቫይረስ የሚያደርሰውን ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖና ጉዳት ለመቀነስ ያለመ ነው ተብሏል።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድም በዚህ ሳምንት ለኢትዮጵያ እና አፍጋኒስታን ድጋፍ ለማድረግ የቀረበውን ሰነድ ተመልከቶ እንደሚያጸድቅ ነው የሚጠበቀው።

ድጋፉ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ባንኩ ለአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ በሚል ባለፈው ሳምንት ካጸደቀው 14 ቢሊየን ዶላር ለሃገራቱ የሚሰጥ መሆኑን የባንኩ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ አስታውቀዋል።

ባንኩ ባለፈው ሳምንት ዓለም ላይ የኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ መቀነስና መከላከል የሚያስችል የ14 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ማፅደቁ ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈም ባንኩ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ትብብርና ከባንኩ የግሉ ሴክተር ዘርፍ ጋር በመሆን በ24 ሃገራት ተግባራዊ የሚደረግ የ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ለመተግበር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.