Fana: At a Speed of Life!

ተመድ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን ማሻሻያ እንዲያደርግ ኢትዮጵያ ጥሪ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን የተሻሻለ፣ ብቁ እና ሊተገበር የሚችል ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ ኢትዮጵያ ጥሪ አቀረበች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት የተከበረውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ የተመድ መስራች አባል የሆነችው ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1945 በስራ ላይ ለዋለው የድርጅቱ ቻርተር ጽንሰ ሐሳቦች ተፈጻሚነት በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኗን ገልጿል።

ለዓለም ሰላምና የጋራ ደኅንነት ካላት ጉልህ አስተዋጽኦ አኳያም÷ ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 1950ዎቹ መጀመሪያ አንስቶ ለተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ከፍተኛ ሚና እየተጫወተች መሆኗን አመልክቷል።

ኢትዮጵያ በተመድ ቻርተር እና መሰረታዊ ጽንሰ ሐሳቦቹ ያሉ የባለብዙ ወገን መርሆዎችን እያከበረች በምትገኝበት ወቅት÷ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን የተሻሻለ፣ ብቁ እና ሊተገበር የሚችል ማሻሻያዎችን እንዲያደርግም ጥሪ ታቀርባለች ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

የዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ለሰዎች አንገብጋቢ ፈተናዎች የተሻለ ምላሽ ለመስጠት ሁሉን አቀፍ፣ አሳታፊ፣ ፍትሐዊና ወካይ ሊሆን እንደሚገባውም በመግለጫው ተገልጿል።

የባለብዙ መስክ አሳታፊነት ከተመድ ቻርተር ምሰሶዎች ጋር የተጣጣመ መሆን እንዳለበትም ነው የተገለጸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.