Fana: At a Speed of Life!

ስኳርና ኬሚካል ከቀይ አፈር ጋር በመቀላቀል ማር ነው ብሎ ለመሸጥ ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ስኳር እና ኬሚካል ከቀይ አፈር ጋር በመቀላቀል ማር ነው ብሎ ለመሸጥ ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ።

ግለሰቡ ሙሉ መኖሪያ ግቢ ተከራይቶ ህገ – ወጥ ተግባሩን ሲፈፅም በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው ፖሊስ በጥርጣሬ ባደረገው ማጣራት ነው።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።

ግለሰቡ መርካቶን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ማር ነው ብሎ ያዘጋጀውን ባዕድ ነገር ሲሸጥ እንደቆየ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከኮሮና ቫይረስ ወረርሸኝ ጋር ተያይዞ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት በሚፈፅሙ እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የክፍለ ከተማው የወረዳ 11 ንግድና ኢንዱስትሪ ፅህፈት ቤት ሃላፊ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.