ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠባቂው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።
የፋሲልን የአሸናፊነት ጎል ታፈሰ ሰለሞን በ 42ኛው ደቂቃ ከሳጥን ውጭ የግል ብቃቱን ተጠቅሞ አስቆጥሯል።
በጨዋታው የአፄዎቹ ተከላካይ ሰኢድ ኩሊባሊ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
ቀን 7 ሰዓት በተደረገ ሌላኛ መርሃ ግብር ሲዳማ ቡና ወልቂጤ ከነማን በእንዳለ ከበደ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል።