ስፓርት

ባህርዳር ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲን 2 ለ 0 አሸነፈ

By Mikias Ayele

October 26, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህርዳር ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በሜዳው እና በደጋፊው ፊት የተጫወተው ባህር ዳር ከተማ በኦሴ ማውሊ እና ፉአድ ፈረጃ ሁለት ጎሎች አዲስ አዳጊውን ለገጣፎ ለገዳዲን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችለዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ባህር ዳር ከተማ ከነበረበት የውጤት ቀውስ ማገገም ችሏል፡፡

10 ሰዓት ላይ መቻል ከኢትዮጵያ መድን ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

በሌላ መርሐ ግብር 10፡00 ላይ በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን መቻልን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡