Fana: At a Speed of Life!

የዜጎች ሰብአዊ እርዳታም ሆነ ጥበቃ ለድርድር አይቀርብም – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዜጎች ሰብአዊ እርዳታም ሆነ ጥበቃ ለድርድር እንደማይቀርብ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ አስታወቁ።

ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት ለማስጠበቅና የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲሁም የመሰረታዊ አገልግሎት አቅርቦትን ለማረጋገጥ ሕገ መንግሥታዊ ተልዕኮውን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

አያይዘውም የዜጎች ሰብአዊ እርዳታም ሆነ ጥበቃ ለድርድር እንደማይቀርብ ጠቅሰው፥ በተመሳሳይ ሁኔታ የትግራይ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታም ሆነ ጥበቃ ለድርድር አይቀርብም ብለዋል።
በሁሉም አካባቢዎች በአስቻጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ሁሉ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማፋጠን መንግስት በትጋት እየሠራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በተረጅዎች ስም የሚመጣ የእርዳታ እህልና መድኃኒት በየትኛውም የሽብር ቡድን እንዲዘረፍ መንግስት አይፈቅድም ያሉት ሚኒስትሩ፥ መንግሥት የዕርዳታ ሥርጭቱን እንደሚቆጣጠር ገልጸዋል።

ይህ ህገ-መንግስታዊ ግዴታው መሆኑን በማንሳትም፥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል እንደሚሰራም አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.