Fana: At a Speed of Life!

የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ማጠናቀቂያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ማጠናቀቂያ መርሐ ግብር በአዳማ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፈንታ ደጀን÷ መንግስት በከተሞች ያሉ ዜጎችን የከፋ ድህነት ለመከላከልና ኑሯቸውን ለማሻሻል፥ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች የደረሱ ጉዳቶችን ለመከላከልና ለማቋቋም እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ለዚህም በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር በ450 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት በ11 ከተሞች ለመተግበር የተቀየሰው የከተሞች ምግብ ዋስትናና ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ላለፉት አምስት ዓመታት ሲተገበር ቆይቶ ፍጻሜ ማግኘቱን ጠቁመዋል፡፡

በዚህም ከ600 ሺህ በላይ ዜጎችን በልዩ ልዩ ዘርፎች በማሳተፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

በመጀመሪያውው ምዕራፍ ፕሮግራም በተሰሩ የከተማ ልማት ሥራዎች፣ በውሃ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በትምህርት ተቋማት ግንባታ፣ በጋራ መፀዳጃ ቤት ግንባታ፣ በከተማ ግብርና እና በተለያዩ አገልግሎቶች በመሰማራት በተሰሩ ሥራዎች ዜጎችን ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡

በአዳማ ከተማ በፕሮጀክቱ ከ26 ሺህ በላይ ዜጎች ታቅፈው በተለያዩ ዘርፎች በመሰማራት ተጠቃሚ መሆናቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.