በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በከተማ ምግብ ዋስትና ፕሮግራም በአማራ ክልል በተለያየ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀን ለአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ አስረክበዋል።
ድጋፉ በተለያዩ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚከፋፈል መሆኑ ተገልጿል፡፡
ድጋፉን ለሚመለከታቸው ተጠቃሚዎች በጊዜው እንዲደርስ የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሠራ ተጠይቋል፡፡
ርዕሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለጹት፥ በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት የተፈናቀለው ሕዝብ ቁጥር ከፍተኛ ነው፡፡
ከአጎራባች ክልሎች በተለያየ ምክንያት በመፈናቀል ወደ ክልሉ የገቡ ተፈናቃዮች ቁጥርም በርካታ ነው ብለዋል።
የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ከፍተኛ ርብርብ ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመው፥ ዛሬ በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የተደረገው ድጋፍም ለዚህ ተግባር አጋዥ ይሆናል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ተፈናቃዮች ተጠቃሚ ሆነው ወደ መደበኛ ኑሯቸው እንዲመለሱ ሁሉም የበኩሉን እንዲያደርግም ጠይቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!