በመከላከያ ሠራዊቱ የተደረገልን አቀባበል ከተነገረን በተቃራኒው ሆኖ አግኝተነዋል- እጃቸውን ለሠራዊቱ የሰጡ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የተደረገልን አቀባበል ከተነገረን በተቃራኒው ሆኖ አግኝተነዋል ሲሉ እጃቸውን የሰጡ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ተናገሩ፡፡
አሸባሪው ህወሓት በደረሰበት ምት መበታተኑን እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊት የሠጡ ታጣቂዎች አረጋግጠዋል።
እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊ የሰጡ ታጣቂዎች እንደገለፁት፥ በመከላከያ ሠራዊቱ የተደረገልን አቀባበል ከተነገረን በተቃራኒው ሆኖ አግኝተነዋል።
መከላከያ ሠራዊቱ ሲማርከን እንደቤተሰቡ ነው የተቀበለን ያሉት የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች፥” እጃችንን በመስጠታችን እድለኞች ነን ቆስለንም እየታከምን ነው” ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!