ቢዝነስ

በ2015 ከቅባት እህሎች ወጪንግድ ከ300 ሚሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት እየተሠራ ነው

By Alemayehu Geremew

October 26, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ዓመት ወደ ውጪ ከሚላኩ የቅባት እህሎች ከ 300 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት እየተሠራ መሆኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ።

የሚኒስትሩ አማካሪ መስፍን አበበ ለፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷ ኢትዮጵያ ከቅባት እህሎች የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ የሚያስችል አሠራር ተዘርግቷል፡፡

የገበያ መዳረሻዎችን ይበልጥ ለማስፋት እና የሚላከውን የምርት መጠን ለማሳደግም በትኩረት ይሠራል ነው ያሉት፡፡

አምራቾች ምርቶቹን በቀጥታ ወደ ውጭ መላክ የሚችሉበት አሠራሮች መመቻቸቱንም ጠቁመዋል፡፡

የቅባት እህል ላኪዎች ምርቶቹን በሰዓቱ እንዲልኩ ማድረግ ከተዘረጋው አሠራር አንዱ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ምርቶቹም÷ ወደ እስራኤል፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ቱርክ እና ሲንጋፖርን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት እንደሚላኩ አረጋግጠዋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የቅባት እና ጥራጥሬ ሰብሎች ልማትና ድኅረ ምርት ዴስክ ኃላፊ ፍስሐ ቶሎሳ በበኩላቸው ÷ በተያዘው የምርት ዘመን ከ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሔክታር በላይ በተለያዩ የቅባት እህሎች መሸፈኑን ገልጸዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን