ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ የስታትስቲክስ ተቋማት ኃላፊዎች ሣይንስ ሙዚየምን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የስታትስቲክስ ተቋማት ኃላፊዎች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ቡድን ሣይንስ ሙዚየምን ጎበኙ፡፡
በጉብኝታቸው በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የቀረቡ የሳይበር ደኅንነት ምርትና አገልግሎቶችን ጨምሮ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮ ቴሌኮምን ምርትና አገልግሎቶችን ተመልክተዋል፡፡
በሣይንስ ሙዚየም የተመለከቷቸው የቴክኖሎጂና የፈጠራ ውጤቶች እንዳስደነቋቸውም ገልጸዋል፡፡
ጎብኚዎቹ ሙዚየሙ ለአፍሪካውያን ትልቅ ኩራት ነው ማለታቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር መረጃ ያመላክታል፡፡