Fana: At a Speed of Life!

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጊዜው ተቋርጦ የነበረውን በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ እንደገና ለማስጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ብሔራዊ ኮሚቴው አስታወቀ፡፡

የኮሚቴው አባላት በተመላሾች ጊዜያዊ መጠለያዎች ጉብኝት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ጉብኝቱን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ÷ መንግስት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ ተግባራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል።

በየመጠለያዎቹ መሠረታዊ አገልግሎት የሚያስፈልጉ የግብዓት አቅርቦት ስለመሟላቱ፣ ለተመላሾቹ ሥልጠና ለመሥጠትና ሥራ ዕድል ለመፍጠር ስለሚቻልበት ሁኔታ እና በቀጣይ ከሳዑዲ ዓረቢያ ለሚመለሱ ዜጎች መጠለያዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ታስቦ የተዘጋጀ ጉብኝት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት 16 ባለድርሻ ተቋማትን የያዘ ብሔራዊ ኮሚቴ በማስተባበር በቅንጅት በተሠራው ሥራ በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ከ71 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገር ቤት መመለስ መቻሉን አስታውሰዋል፡፡

በቅርቡ ዜጎችን ለመመለስ በሁለተኛው ዙር በጊዜያዊ መጠለያ አካባቢ የተደረገው ጉብኝት ጠቃሚ ግብዓት የተገኘበት መሆኑም ተገልጿል፡፡

ለጊዜው ተቋጦ የነበረው ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ  ሥራ በሁለት ሳምንት ውስጥ እንደሚጀመር ተጠቁሟል፡፡

በጉብኝቱ ላይ÷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የሥራ ፈጠራና ክኅሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.