Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ብሪታንያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በጋራ የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን አሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ብሪታንያ በአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የጀመሩትን የጋራ ስራ አጠናክረው እንደሚቀትሉ አረጋገጡ፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ የብሪታንያ የኮፕ26 የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ አምባሳደር ጃኔት ሮጋን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እየሰራች ያለችውን ስራ በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በግብጽ ሻርማል ሸክ በሚካሄደው ኮፕ 27 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይም በርካታ ለዓለም የምታካፍላቸው ተሞክሮዎች አሉም ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡

በዚህም የአረንጓዴ አሻራ ፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ፣ የታዳሽ ሃይል እንዲሁም መሰል ስራዎችን በመድረኩ ለዓለም ለማሳወቅ ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

ብሪታንያ በዘርፉ ያላትን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት የገለጹት የብሪታንያ የኮፕ 26 የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ አምባሳደር ጃኔት ሮጋን ፥ ኢትዮጵያ ለዓለም ተሞክሮ የሚሆን ስራ እየሰራች መሆኗን እንገነዘባለን ብለዋል፡፡

በግብጽ በሚካሄደው ጉባዔም ብሪታንያ ለኢትዮጵያ የተለያዩ ድጋፎችን ታደርጋለችም ነው ያሉት አምባሳደሯ፡፡

ሁለቱ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ዙሪያ የጀመሩትን ዉጤታማ ተግባራት ለማስቀጠልና የኢትዮጵያን ውጤታማ ተግባራት ለማገዝ ብሪታንያ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ማረጋገጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.