ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በዱከም የሚገኘውን የሴራሚክ ፋብሪካ ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በኦሮሚያ ክልል ዱከም ከተማ የሚገኘውን የሴራሚክ ፋብሪካ ጎበኙ፡፡
ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት÷ በርካታ የሴራሚክ ምርት ክምችት ቢኖርም ለገበያ ሳይቀርብ መቀመጡን ተመልክተናል፡፡
እንደዚህ አይነት ምርትን የመደበቅና የገበያ አሻጥር በሚፈጽሙ አምራቾች ላይ የሚወሰደው እርምጃ እንደሚጠናከርም አረጋግጠዋል፡፡
የፋብሪካው ኃላፊዎች ለቀረበላቸው ጥያቄ በቂ ምላሽ ባለመስጠታቸው በአፋጣኝ ወደ ሕግ እንዲቀርቡ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡
በምንተስኖት ሙሉጌታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!