የከፍተኛ ሊግ ውድድር ህዳር 17 ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ሊግ ውድድር ህዳር 17 ቀን 2015ዓ.ም እንደሚጀምር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
የከፍተኛ ሊግ ውድድሩ ህዳር 3 ቀን 2015ዓ.ም እንደሚጀምር መገለፁ ይታወሳል፡፡
ሆኖም ውድድሩ በተጠቀሰው ቀን እንዲጀመር መወሰኑ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የዝግጅት ጊዜ እንደሚያጥራቸው የክለብ ተወካዮች ገልፀዋል፡፡
በመሆኑም ውድድሩ እንዲራዘም ከተሳታፊ ክለቦች የተነሳውን ጥያቄ ከግምት በማስገባት የውድድሩ መጀመሪያ ጊዜ ላይ ሽግሽግ መድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት ክለቦች እስከ ህዳር 9 ቀን 2015ዓ.ም ድረስ የሚጠበቅባቸውን የዳኞች እና ታዛቢዎች እንዲሁም የምዝገባ ክፍያ በማጠናቀቅ ውድድሩ ህዳር 17 ቀን እንዲሆን ውሳኔ መተላለፉን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡