የሀገር ውስጥ ዜና

በርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራር የግብርና ልማት ሥራዎችን ጎበኙ

By Meseret Awoke

October 27, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራር አይሳኢታ አፋንቦ ወረዳዎች የተከናወኑ ያሉትን የግብርና ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም የተለያዩ የግብርና ልማት ስራዎችን፣ የወጣቶችና የሴቶች ማህበር የግብርና ስራ ልማትንም ነው የጎበኙት፡፡

በዚህ ወቅት ወጣቶችን በማበረታታት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ።

ጉብኝቱ በቀጣይ በተለያዩ አካባቢዎች እንደሚቀጥል የአፋር ብዙኃን መገናኛ ዘገባ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!