የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ከፊታችን ጥቅምት 19 እስከ 22 ቀን ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወጣት መሪዎች የሚሳተፉት ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ ከጥቅምት 19 እስከ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀሳብ አመንጪነት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፥ የፓን አፍሪካኒዝም ሀሳብን ለማበልፀግ የሚያስችል መሆኑን የጉባኤው አስተባባሪዎች ገልፀዋል።
ጉባኤው ታሪካዊ ዳራ ያለውን የአፍሪካ ወጣቶች የወንድማማችነት ህብረት የሚያጠናክር እና በአፍሪካ ወጣቶች መካከል ከፍተኛ ትስስር እንደሚፈጥር ተጠቁሟል፡፡
ተሳታፊ ወጣቶች ወደ አዲስ አበባ መግባት የጀመሩ ሲሆን፥ በርካታ ቀደምት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጭምር ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተጠቅሷል።
በአፍሪካ ህብረት በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከመላው አህጉሪቱ የተወጣጡ ወጣት መሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን፥ አህጉራዊ የሆነውን ሰፊ እይታ እንዲላበሱ ጥረት እንደሚደረግ ተገልጿል።
ጉባኤው ከአረንጓዴ ዲፕሎማሲ መርሐ ግብር በተጨማሪ ለአፍሪካዊ ወንድማማችነት ትልቅ አቅም መፍጠር የሚችል ጉባኤ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡
መድረኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተዘጋጀ መሆኑንም ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡