Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ባለሃብቶች እንዲገቡ በማድረግ የተሻለ ኢንቨስትመንት እንዲኖር እየተሰራ ነው – አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የውጭ ባለሃብቶች እንዲገቡ በማድረግ የተሻለ ኢንቨስትመንት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ አይዞን ማኒፋክቸሪንግ እና ሸንተዝ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅት እንዳሉትም ፥ ገቢ ምርቶችን ስትራቴጂክ በሆኑ የአገር ውስጥ ምርት ለመተካት በሚደረገው ሂደት ውስጥ ጥራት፣ ዋጋ እና የማስረከቢያ ጊዜ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የውጭ ባለሃብቶች እንዲገቡ በማድረግ የተሻለ ኢንቨስትመንት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በተለይም በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በማዕድንና በአይሲቲ ዘርፎች እንደሀገር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነም ነው ያነሱት።

የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ስምምነት ወደ ስራ እየገባ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በኃይል፣ በመንገድ፣ በባቡር የተጀመሩ ግንኙነቶች በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን ለማቀራረብና ኢኮኖሚውን በማሳደግ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

አምራች ድርጅቶች ከውጪ ምንዛሬ አቅርቦት፣ ከማምረቻ መሬት፣ ከኃይል እና ከንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

በተጀመረው የኢትየጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ መሰረት ለገጠሟቸው ችግሮች መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው የተገለጸው፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.