Fana: At a Speed of Life!

የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ነገ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ምዕራፍ 12 ፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በነገው ዕለት ይጀመራል።

የምዕራፍ 9፣ የምዕራፍ 10 እና የምዕራፍ 11 አሸናፊዎች የሚሳተፉበት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር፥ 14 ተወዳዳሪዎች በሁለት ምድብ ተከፍለው የሚወዳደሩበትን ዘፈን ያቀርባሉ፡፡

በነገው የመጀመሪያ ሣምንትም የምድብ አንድ ሰባት ተወዳዳሪዎች፥ ዳንኤል አዱኛ፣ ኤደን ገ/ትንሳኤ፣ አሉላ ገ/አምላክ፣ አቤል ታረቀኝ፣ ዘላለም ታደሰ፣ ዮርዳኖስ ደስይበለው እና ገረመው ገ/ጻዲቅ ተሳታፊ ድምፃውያን ሲሆኑ፥ በሁለት ዙር ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

በሙዚቃ ባለሙያዎች እና በተመልካቾች የአጭር የፅሁፍ መልዕክት የሚዳኘው የፋና ላምሮት የድምፃውያን ውድድር ቅዳሜ ሲጀምር ተመልካቾች በስልኮቻቸው ያለገደብ መልዕክት በመላክ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር አንደኛ ለሚወጣ ድምፃዊ የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፥ ፕሮግራሙ ከነገ 6 ሰዓት ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን እና በተለያዩ የዲጂታል መዲያዎች በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

የተደበቁ ባለተሰጥዖ ድምፃውያንን ወደመድረክ በማምጣት እና የሙዚቃውን ዘርፍ በማበረታታት ረገድ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የራሱን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.