Fana: At a Speed of Life!

ለሀገራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት አወንታዊ ሚና ይጫወታል -የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለምታካሂደው ሀገራዊ ምክክር የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት አወንታዊ ሚና እንደሚጫወት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረግን ውይይት ለማስቀጠል ከፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያየ ነው።

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ከዚህ ቀደም የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን አስታውሰው የፓርቲዎቹ ግንኙነት እንዲጠናከር ውይይቶች እንደሚካሄዱ ገልጸዋል።

በመድረኩ የተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በበኩላቸው÷ የፖለቲካ ፓርቲዎች አለመግባባት በሀገር አንድነት ላይ ጥላ የሚያጠላ ስለሆነ መመካከርና ውይይቱ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውበሸት አየለ እንደተናገሩት÷ ኢትዮጵያ ምንም እንኳን የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን ብትከተልም፥ የአንድ ፓርቲ ተፅዕኖና አካሄድ አለው መባሉን አንስተዋል ፡፡

ይሁንና ፓርቲዎች ቢቀራረቡ እና ቢነጋገሩ ይህን መልክ መቀየር ይቻላል በሚል ከ53 ፓርቲዎች 43ቱ የፈረሙበት ሰነድ ለተግባራዊነት መዘጋጀቱን አስታውሰዋል ።

ይህ በፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ውይይት ከሰመረ በብሔራዊ ደረጃ ለተቋቋመው የምክክር ኮሚሽንም አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሚሆን ነው የተናገሩት።

በፀጋዬ ወንድወሰን እና አፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.