Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በመጋዘን አከማችቶ ሲጠቀምበት የነበረው ስንዴ ለህዝቡ ተከፋፈለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በመጋዘን አከማችቶ ለተዋጊው ቀለብ ሲጠቀምበት የነበረው ስንዴ ለህዝቡ ተከፋፈለ፡፡

ከአሸባሪው ህወሓት ነፃ የወጡ ነዋሪዎች የመከላከያ ሠራዊት  የህዝቡን ደህንነት በመጠበቅ እና አሸባሪ ቡድኑ ለጦርነት አላማ ሊያውለው የነበረውን የእርዳታ እህል በመከፋፋላቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልፀዋል።

የዕዙ ስነ-ልቦና ግንባታ ኃላፊ እንደገለፁት መከላከያ ሠራዊት የበይ ተመልካች ለነበረው የኮረም ከተማ ነዋሪዎች የዕርዳታ እህል በማደል ለህዝብ ደራሽ መሆኑን በተግባር አሳይቷል ብለዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ጁንታው በሰብአዊ ድጋፍ በእርዳታ ስም ወደ ትግራይ ክልል ሲገባ የነበረውን ስንዴ በመጋዘን አከማችቶ ለተዋጊ ሰራዊቱ ቀለብ ሲጠቀምበት የነበረውን የመከላከያ ሰራዊት በመቆጣጠር ጁንታው በሰብአዊ ድጋፍ  ስም ወደ ትግራይ በማስገባት ሲጠቀምበት የነበረውን 120 ኩንታል ስንዴ ለአባወራዎችና እማወራዎች በማከፋፈል ሰራዊቱ ህዝባዊነቱን በተግባር አረጋግጧል ነው ያሉት።

ነዋሪዎችም ሰራዊቱ ላደረገላቸው በጎ ተግባር ያላቸውን ምስጋና ገልፀው ባሳለፉት ጊዜያት በሽብር ቡድኑ ምክንያት ለረሃብና እንግልት ተጋልጠን ቆይተናል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.