Fana: At a Speed of Life!

በህጻናት ላይ የሚከሰት የስኳር ህመም ምልክቶች እና መፍትሄው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስኳር ህመም በሰውነት ውስጥ ምግብን በተለይም ስኳርን (ካርቦሃይድሬትን) ወደ ሰውነታችን ሀይል የመቀየር ችሎታ ላይ ችግር የሚፈጥር ነው፡፡

የስኳር ህመም አዋቂዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ህጻናትም ላይ እንዲሁም በየትኛውም የእድሜ ክልል ሊከሰት ይችላል።

የአይነት አንድ ስኳር ህመም ደግሞ በየትኛውም የህጻናት እድሜ ሊከሰት ቢችልም ከ4 እስከ 6 አመት እና ከ10 እስከ 14 አመት ባለው እድሜ ክልል የመከሰት ዕድሉ እንደሚጨምር ይነገራል፡፡

ስኳር በዘር የመተላለፍ እድል ሲኖረው ከአይነት አንድ ይልቅ አይነት ሁለት ስኳር በዘር የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው።

በህጻናት ላይ የሚከሰት የስኳር ህመም ሽንት ቶሎ ቶሎ መሽናት በተለይም በምሽት ላይ፣ ተኝቶ ሽንት ማምለጥ፣ ውሃ ቶሎ ቶሎ መጠጣት፣ ምግብ ቶሎ ቶሎ መብላት፣ የድካም ስሜት፣ ክብደት መቀነስ ወይም እድገት ማቆም፣ በሽታ የመከላከል አቅም መቀነስ፣የማቅለሽለሽ ስሜቶች አሉት።

የዓይነት አንድ የስኳር በሽታን ለመመርመር በአንጻራዊነት ቀላል ሲሆን÷ ምርመራዎቹም የስኳር መጠን ምርመራ፣ የA1C ምርመራ ፣ ከቁርስ በፊት በሚደረግ የስኳር መጠን ምርመራ፣ ለ8 ሰዓት ያህል ምግብ ሳይበላ የሚደረግ ምርመራን ያካትታል።

ለዓይነት አንድ የሚሰጡት የስኳር በሽታ ሕክምናዎች ደግሞ ኢንሱሊን መውሰድ፣ የስኳር መጠንን መከታተል፣ ጤናማ ምግቦችን መመገብ፣ አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ መሆናቸውን ከጥቁር አንበሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ገፅ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.