የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ከሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ በኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ፋሃድ አልሁማይዳኒ ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸው ወቅትም በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ መምከራቸውን አስታውቀዋል።
ከዚህ ባለፈም የሳዑዲ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ለማድረግ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት መግባባታቸውንም ነው የገለጹት።