Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የምርጥ ዘር ፍላጎትን ለማሟላት 25 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በግብርናው ዘርፍ ለሚያስፈልገውን የምርጥ ዘር ፍላጎት ለማሟላት 25 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚያስፈልግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል፡፡

በርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ የተመራ ልዑካን ቡድን በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢ ጠህናን ወረዳ በ 2 ሺህ 600 ሄክታር መሬት ላይ እየተባዛ ያለ የምርጥ ዘር ብዜት ማሳ ጎብኝቷል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሃይለማርያም ከፍያለው በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ የክልሉን የምርጥ ዘር ፍላጎት ለመሸፈን 25 ሺህ መሬት ያስፈልጋል፡፡

ባሳለፍነው ዓመት በ12 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የዘር ብዜት መከናወኑን አንስተው በክልሉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የበቆሎ ምርጥ ዘር ፍላጎትን ለመሸፈን መቻሉንም ገልጸዋል፡፡

የክልሉን የምርጥ ዘር ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን የዘር ማባዣ መሬት ፍላጎትን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በበላይነህ ዘለዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.