Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በክልሉ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በዱብቲ እና ሎጊያ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በአካባቢው የጎርፍ አደጋ እያስከተለ ያለውን ችግር ለመቅረፍ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የታቀደውን የምርታማነት አቅጣጫ ተከትሎ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የስንዴ ማሳዎችን ጨምሮ የተለያዩ ሰብሎች የሚመረቱባቸውን አካባቢዎች መጎብኘታቸውንም የርዕሰ መስተዳድሩ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.