8ኛው የኢትዮ- ሩሲያ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባዔ የፊታችን ታህሳስ ወር በአዲስ አበባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ስምንተኛው የኢትዮ- ሩሲያ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባዔ የፊታችን ታህሳስ ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የኢኮኖሚ ጉባዔው ሰብሳቢ በለጠ ሞላ ÷ ስምንተኛው የኢትዮ- ሩሲያ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባዔን ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዶክተር በለጠ የጉባዔው አዘጋጅና ተሳታፊ ተቋማት አመራሮች ጋር እየተደረጉ ባሉ ቅድመ ዝግጅቶች ላይ ተወያይተዋል፡፡
የኮሚቴ አባላቱ ቀደም ሲል በተደረጉ ውይይቶች በተደረሱ ስምምነቶችና የሥራ አቅጣጫዎች መሰረት ሪፖርቶችን አቅርበዋል፡፡
ዶክተር በለጠ በቀጣይ ተሟልተው መቅረብ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንዲሠራ ማሳሰባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ፒተርሰበርግ ላይ በተካሄደው ሰባተኛው የሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉባዔ በተፈረሙ ስምምነቶችና የጋራ አቋሞችመሰረት የተጠናቀቁ ሠነዶች ወደ ሥራ ሊገቡ ይገባል ብለዋል፡፡
አዲስ የሚፈረሙ ስምምነቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁና ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ ከሩሲያ የሚገኙ ድጋፎችን የሚያስገኙ ስምምነ